የጽ/ቤቱ ሥልጣንና ተግባር

  1. የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽንን በበላይነት ይመራል፤ያስተባብራል ፤ ይደግፋል፤
  2. አገራዊ የቤቶች ልማትና አስተዳደርን የሚመለከቱ ፖሊሲዎች፤ዝርዘር የህግ ማዕቀፎች እንዲሁም ስታንዳርድ በከተማዋ ተፈጻሚ መሆናቸውን ያረጋግጣል፤ የማሻሻያ ግብዓቶች ያሰባስባል፤ ለሚመለከተው አካል ያስተላልፋል፤ ተግባራዊነቱንም ይቆጣጠራል፡፡
  3. በመንግስት አስተባባሪነት፣ በመንግስትና በግል አጋርነት፣ በመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበራት፣ የግል ቤት አልሚዎች እና ሪል ስቴቶችን እና በሌሎች አማራጭ የቤት ልማት ፕሮግራሞችን ለማከናወን እና አጠቃላይ አቅጣጫ ለመቀየስ የሚያስችል ጥናቶችን ያጠናል፣ ያስጠናል፣ስልትና ስታንዳርድ ያዘጋጃል፣ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፣ ሲፈፀም አፈፃፀሙን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤
  4. የሚያስተዳድራቸውን ቤቶች መረጃ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ይይዛል፤ የመኖሪያ ቤት አይነቶችን መደብ እና ደረጃ ያወጣል፤የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ይሰጣል፤
  5. በጋራ መኖሪያ ቤት ማህበራት እንዲመሠረቱና በህግ አግባብ ተልኳቸውን እንዲወጡ ያበረታታል፤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር ችግሮቹ እንዲወገዱ ያደርጋል፤
  6. በአነስተኛና መካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ነዋሪዎች በተለይም ሴቶችና አካል ጉዳተኖች በቤት ልማት ፍትሃዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያሠራር ስርዓት ይዘረጋል፤
  7. የቤት ልማቱ ስራ ከድህነት ቅነሳ እና ከስራ እድል ፈጠራ ጋር የተቀናጀ እንዲሆን ያደርጋል፣ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
  8. አግባብ ባለው ህግ መሰረት ነዋሪው ከአቅሙ ጋር የተመጣጠነ መኖሪያ ቤት እንዲሠራ በመንግስትና በግል ባለሀብቶች አጋርነት እና በሌሎች የቤት ልማት አማራጮችን በመጠቀም የቤት ልማት ማካሄድ የሚችሉበት አጠቃላይ አቅጣጫ ለመቄስ የሚያስችሉ ጥናቶችን ያካሂዳል፣ ስርዓት ይዘረጋል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
  9. በቤት ልማት ዘርፍ የሚሠማሩ አካልት ተቀናጀተው የሚሠሩበትን የአሠራር ስርዓት ይዘረጋል፤ ድጋፍ ያደርጋል፤ አፈጻጸሙን ይቆጣጠራል፤
  10. ከቤት ሽያጭ፣ ኪራይ እና የመሳሰሉት ተግባራት ላይ ጤናማ የገበያ ስርዓት እንዲኖር የሚያስችል ጥናቶችን ያጠናል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፤
  11. በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ወቅታዊ የቤት ፍላጎትና አቅርቦት፣ አጠቃላይ የተመዝጋቢዎች እና የቤት መረጃ በዝርዝር ይይዛል፤ ወቅታዊ ያደርጋል፤ ለዕጣ ብቁ የሆኑ ቆጣቢዎችን በመለየት መረጃውን ለሚመለከተው አካል ያስተላልፋል፤ አሰፈላጊ ሆኖ ሲገኝ አዲስ ቤት ፈላጊዎችን ይመዘግባል፤
  12. የቤት ፍላጎትና አቅርቦት መለየት የሚያስችል ዝርዝር ጥናት ያከናውናል፤ የቤት አቅርቦት ክፍተቶችን በመለየት የመፍትሔ ኃሳቦችን ያመነጫል፤ ለሚመለከተው አካል በማቅረብ ያሰወስናል፣ ይተገብራል፤ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፤
  13. ቤቶች በልማት ወይም በተፈጥሮ ወይም በሰው ሰራሽ አደጋ ምክንያት በሚፈርሱበት ወቅት አስፈላጊው መረጃ ከሚመለከተው አካል ጋር ይለያል፤ ያጣራል፤ ያደራጃል፤ ቤት ለፈረሰባቸው አካላት ምትክ ቤት እንዲሰጣቸው ለሚመለከተው አካል መረጃዎችን ያስተላልፋል፤
  14. የከተማ አስተዳደሩ ንብረት የሆኑ የመኖሪያ፣ ንግድ፣ ለኪራይ አገልግሎት የተገነቡ ቤቶች እንዲሁም የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በፍትሃዊነት ያስተዳድራል፤ ያከራያል፤ እንዲጠገን ያደርጋል፤
  15. የከተማ አስተዳደሩ ንብረት የሆኑ የመኖሪያ፣ ንግድ ቤቶች፣ ለኪራይ አገልግሎት የተገነቡ ቤቶች እንዲሁም የጋራ መኖሪያ ቤቶች በህገ ወጥ መንገድ ከያዙት አካላት ያስለቅቃል፤
  16. የቤት አልሚ መረጃዎችን ይሰበስባል፤ ይተነትናል፣ ያደራጃል፤ ለሚመለከታቸው አካላት ያሠራጫል፡፡