በልደታ ክፍለ ከተማ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ዝርዝር አገልግሎቶች

1. በተለያዩ አማራጮች የመኖሪያ ቤቶችን የማልማት አገልግሎት መስጠት፣
  • በተለያየ የቤት ልማት ፕሮግራም የቤት ፈላጊዎች ምዝገባ አገልግሎት፣
  • የጋራ ህንፃ መኖሪያ ቤት ህ/ሥ/ማ/አባላት ምዝገባ አገልግሎት፣
  • ከመንግስት ጋር በአጋርነት በቤት ልማቱ ዘርፍ የሚሰሩ ባለሃብቶችን የመመዝገብና የመመልመል አገልግሎት፣
  • የቤት አልሚዎች የሚያቀርቡትን ፕሮፖዛሎች በመገምገምና ውል የማዋዋል አገልግሎት፣
  • የለማ መሬት በተለያዩ ፕሮግራም በአማራጭ የተደራጁ ማህበራት እና የቤት አልሚ ባለሀብቶች የማስረከብ አገልግሎት፣
  • ለቤት ልማት ፕሮግራም የተገኘ የፋይናንስ ብድር የማስመለስ አገልግሎት፣
  • ከጥቃቅን አነስተኛ ቢሮ የሚላኩ ኢንተርፕራይዞችን ወደ ስራ የማሰማራት አገልግሎት፣
  • የቤት ልማት ጥናቶችን የማጥናት እና የመኖሪያ ቤት አይነቶችን በጥናት በመለየት፣ መደብና ደረጃ የማውጣት አገልግሎት፣
  • ከቤት አልሚዎች እና ከነዋሪዎች የሚቀርቡ ቅሬታና አቤቱታዎችን በመቀበል ምላሽ የመስጠት አገልግሎት፣
2. የመንግስት ቤቶችን ለዜጎች በፍትሃዊነት ማስተላለፍ አገልግሎት፣
  • በኪራይ የጋራ መኖሪያ ቤት የተመደበላቸዉን አካላት ዉል የማዋዋል አገልግሎት፣
  • በልማት፣ በተፈጥሮ እና በሰዉ ሰራሽ አደጋ ምክንያት ለሚነሱ ተነሺዎች ምትክ ቤት የመመደብ አገልግሎት፣
  • የሚቀርብ የቤት ቅይይር ጥያቄን በመቀበል ከመመሪያ አንፃር በማጣራት ምላሽ የመስጠት አገልግሎት፣
  • በተላለፉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ ከፍርድ ቤት የሚመጡ የማስረጃ ጥያቄዎችን ተቀብሎ ምላሽ የመስጠት አገልግሎት፣
  • ከተላለፉ አምስት አመት በሞላቸዉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ አምስት አመት ስለመሙላቱ የሚቀርብ የማስረጃ ጥያቄን ተቀብሎ ምላሽ የመስጠት አገልግሎት፣
  • በተላለፉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ የሚቀርቡ የዉሃና የመብራት አገልግሎቶችን ተቀብሎ ምላሽ የመስጠት አገልግሎት፣
  • በተላለፉ ቤቶች የሚቀርቡ ቅሬታ፣ አቤቱታዎችና ክሶች በመቀበል ምላሽ የመስጠት አገልግሎት
3. የመንግስት ቤቶችን ማስተዳደር አገልግሎት፣
  • በኪራይ የተሰጡ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን የኪራይ ውል ማደስ አገልግሎት፣
  • የአደራ እና የማካካሻ ጥያቄዎችን ተቀብሎ መመሪያው በሚፈቅደው መሰረት ምላሽ የመስጠት አገልግሎት፣
  • የቤት እድሳትና ጥገና ጥያቄ ተቀብሎ የማስተናገድ አገልግሎት፣
  • የባለጉዳዮችን አቤቱታ በመቀበል የጥያቄውን አግባብነት ከመመሪያ አንፃር በማጣራት ምላሽ የመስጠት አገልግሎት፣
  • ከመንግስት ቤቶች ጋር ተያይዞ ከተለያዩ አካላት የሚቀርቡ ክሶችን በመቀበል መረጃዎችን በማጣራት ምላሽ የመስጠት አገልግ