የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
ከተማችን አዲስ አበባን ሁሉም የሚለማባትና ለኑሮ የተመቸች ሞዴል ከተማ ለማድረግ በሚደረገው ከተማ አቀፍ ጥረት መኖሪያ ቤት የግድ ብቻ ሳይሆን የነዋሪዎች ህይወት መሻሻል፣ የህልሞች እና እድሎች መሳካት ሁሉ መሰረት መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮም ቤቶችን በመገንባት፣ በማስተላለፍና በማስተዳደር ይህንን ቁልፍ የሆነ ሰው ልጆች ፍላጎትና የልማት መሰረት በከተማ ደረጃ ለመመለስ ተልዕኮ ተሰጥቶት እየሰራ ያለ ተቋም ነው፡፡ ከዚህ አንጻር በርካታ ስራዎችን ሰርተናል፡፡ ተግባሮቻችንም ከአሁኑ ትውልድ ፍላጎት የመነጩ ብቻ ሳይሆን የነገን ፍላጎት ታሳቢ ያደረጉ የከተማችንን ተመራጭነትን የሚያሳድጉና ከፍታን የሚያጎናጽፉ እንዲሆኑ ታስቦ እየተከናወኑ የሚገኙ ናቸው፡፡ በከተማዋ ያለዉን ከፍተኛ የሆነ የመኖሪያ ቤት ፍላጎት ለማሟላት ጥራት ያለውና ወጪ ቆጣቢ ቤት በማስገንባት፣ በፍትሐዊነት እንዲተላለፍ በማድረግ፤ ቀልጣፋና ውጤታማ የቤት አስተዳደር ስርዓት በመዘርጋትና በመተግበር የከተማዋ ነዋሪዎችን ተጠቃሚነትን ማሳደግና በዚህም ህይወታቸው እንዲሻሻል፣ ህልማቸውን እንዲያሳኩና እድሎችን እንዲጠቀሙ የተልዕኳችን እምብርት አድርገን እየሰራን ነው፡፡ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ የመጣውን የመኖርያ ቤት ችግር በዘላቂነት ለመፍታትም የተለያዩ ስልቶችን ቀይሰን እየሰራን እንገኛለን፡፡
በቀጣይም ተቋማዊ ለውጥ በማድረግ አሰራሮችን በማዘመንና በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት በመስጠት የተገልጋዮቻችንን ፍላጎት በተሻለ መልኩ ለመመለስ ዝግጁ መሆናችንን እንገልጸለን፡፡ በዚህ ሁሉ ሂደታችን ላስመዘገብናቸው ስኬቶቻችን የነዋሪዎችና የባለድርሻ አካላት አስተያየትና ተሳትፎ ወሳኝ ሚና ነበረው፡፡ ወደፊት በሚኖረን ጉዞም እንደተለመደው ሁሉ በተግባሮቻችን እንድትሳተፉ፣ እውቀታችሁን እንድታካፍሉን እና ሃሳብ እንድትሰጡ እናበረታታለን፡፡ በጋራ፣ሁሉንም ያካተተች፣ለሁሉም የበለፀገች፣ የነገን ትውልድ የዋጀች ከተማና የመኖርያ አካባቢን መፍጠር እንችላለን!!
አቶ ገመቹ ጌታቸዉ , የልደታ ክ/ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ