ዜና | Oduu | News
የልደታ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት የመሬት እና ግንባታ ጉዳዮች ዘርፍ ኮሚቴ የመስክ ምልከታና ሱፐርቪዥን አካሄደ፡፡

የልደታ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት የመሬት እና ግንባታ ጉዳዮች ዘርፍ ኮሚቴ የቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤት ላይ ሱፐርቪዥን እና መስክ ምልከታ አካሂዷል፡፡ የተከበሩ አቶ ታደሰ ገብሬ የመሬት እና ግንባታ ጉዳዮች ዘርፍ ኮሚቴ ሰብሳቢ ተቋሙ ከዚህ ቀደም ከነበረው አሰራር በብዙ መልኩ የተለወጠ መሆኑን እና የቤት ጥያቄ ይዘው የሚመጡትን ደንበኞች ሳይጉላሉ እንዲስተናገዱ በየወረዳ የነበረውን አገልግሎት ፕሮግራም በማውጣት በየቀጠናቸው በተያዘላቸው ቀን እንዲመጡና እንዲስተናገዱ መደረጉ የሚበረታታ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ የቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤት አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን በወረዳ 189 ባለሙያ ይሰጥ የነበረውን አገልግሎት በክፍለ ከተማ አንድ ማዕከል ከሆነ በኋላ ቴክኖሎጂን ተግባራዊ በማድረግ 21 ባለሙያዎችን በመጠቀም የተቀላጠፈ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን እና ብልሹ አሰራርን የማስቀረት ስራ መሰራቱን የፅ/ቤቱ ሃላፊ አቶ ገመቹ ጌታቸው ገልፀው ምክር ቤቱ የሚያደርገው ክትትል እና ቁጥጥር ውጤታማ በመሆኑ ድጋፉ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል በማለት ተናግረዋል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለም ዘርፍ ኮሚቴው በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 የሚገኘውን ባለ 25 ወለል እና በወረዳ 6 ባለ 4 ወለል በበጎ ፍቃድ እየተገነቡ ያሉትን ህንፃዎች በመስክ ምልከታ የተመለከተ ሲሆን በምልከታውም በበጎ ፍቃድ የሚሰሩት ህንፃዎች ከታሰበው በላይ ውጤታማ መሆናቸውን ክቡር ሰባሳቢው አንስተው መንግስት የድሃውን ማህበረሰብ የቤት ጥያቄ በአጭር ግዜ መፍታት እንደሚችል ማሳያ ነው በማለት ተናግረዋል፡፡ የቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤት አገልገሎትን የተቀላጠፈ ለማድረግ ቴክኖሎጂን ተግባራዊ እያደረገ ቢሆንም አሁንም ከስራ ሰዓት በፊት በጠዋት የሚመጡ ባለጉዳዮች ስላሉ ተከታትሎ መፍትሄ መስጠት ይኖርበታል በማለት የተከበሩ አቶ ታደሰ ገብሬ ተናግረዋል፡፡

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
"የነዋሪዎቻችንን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል አስተዳደሩ በቁርጠኝነት ይሰራል!":- ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ

በልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመፍታት የሚያስችል የውይይት መድረክ ተካሄደ። በዛሬዉ እለት በተካሄደው መድረክ ላይ በመኖሪያ ቤት የተፈጠረውን የመልካም አስተዳር ችግር በተመለከተ በቀጣይነት መፍታት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ግለፀኝነት ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ተገልጿል። የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ እንደገለጹት የከተማው ብሎም የክ/ከተማው አስተዳደር የከተማዋን ነዎሪዎች የቤት ተጠቃሚ ለማድረግ በሰው ተኮር ስራዎች በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ገልፀው በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አንስተዋል። ወ/ሮ ልዕልቲ አክለው እንደገለፁት የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት ባለሀብቶችን በማስተባበር፤ እጅግ የተጎሳቀሉና ምቹ ያልሆኑ ቤቶችን በማደስ፤ በሎው ኮስት፣ በኮንደሚኒየም ቁጠባ አማራጭ፣ በማህበር ግንባታ፣ በመንግስትና የግሉ ዘርፍ ትብብር፣ በህገወጥ መንገድ የተያዙ የመንግስት ቤቶችን በማስለቀቅ የቤት ችግሩን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ግንዛቤ አስጨብጠዋል። በክ/ከተማችን በኢኮኖሚ እንዲሁም በአቅም ማነስ መሰረታዊ ፍላጎታቸውን ሳያሟሉ ለችግር የተጋለጡ በርካታ ነዋሪዎች በመዲናዋ መኖራቸውን ገልፀዉ አስተዳደሩ ሰው ተኮር የ90 ቀን ዕቅዶችን በማዘጋጀት ችግሮችን ለመፍታት ርብርብ እያደረገ መሆኑን ወ/ሮ ልዕልቲ ገልፀዋል። ወ/ሮ ልዕልቲ አክለው የነዋሪዎቻችን የቤት ጥያቄዎች ውዝፍ በመሆናቸው ሁሉንም ችግሮችን በአንድ ጊዜ መቅረፍ ባይቻልም ደረጃ በደረጃ እየቀረፍን የነዋሪዎቻችንን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል አስተዳደሩ በቁርጠኝነት እየሰራ ነው ብለዋል። አቶ ገመቹ ጌታቸው የክ/ከተማው ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ በበኩላቸው የከተማው ውስን ሀብት የሆነው ከመንግስት ቤቶች ባሻገር የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ ከሚያስችሉት አንዱ የሆነው የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ ቆጣቢ ነዋሪዎች የከተማ አስተዳደሩ ያዘጋጀውን ይህን አማራጭ ተጠቅመው በማህበር በመደራጀት እና በመቆጠብ የቤት ባለቤት መሆን የሚችሉ መሆኑን ገልፀዋል። የልደታ ክ/ከተማ መልካም አስተዳደር ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ በላይነህ ሙሉጌታ በመድረኩ ላይ እንዳሉት ከመኖሪያ ቤት ጠያቂዎች ጋር የተደረገው የግንዛቤ መፍጠር ስራ በአጠቃላይ የቤት ማስተላለፍና አስተዳደር በተመለከተ የነበረውን የተዛባ አመለካከት የሚያስተካክል መድረክ መሆኑን ጠቁመዋል። በመጨረሻም የውይይት መድረኩ ከተሳታፊዎች አስተያየት ተሰጥቶበት በመግባባት ተጠናቋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክፍለ ከተማ 106 የቀበሌ ቤቶችን ጧሪና ደጋፊ ለሌላቸው አቅመ ደካሞች፣ የአካል ጉዳተኞች እና የአገር ባለውለታዎች ለሆኑ እና እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ የከተማችን ነዋሪዎችን ለይተን በእጣ አስተላለፈ።

ከህዝብ ጋር ባደረግነው ውይይት የተሰጡንን ጥቆማዎችን ጭምር ተጠቅመን ባደረግነው ማጣራት የለየናቸውን ነዋሪዎቻችንን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ፣ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገባ የተዘነጉ፣ ጧሪና ደጋፊ የሌላቸውን አቅመ ደካማ ወገኖችን እንባ በማበስ እና ከነበሩበት አስከፊ ሕይወት በመታደግ ነገን በተስፋ እንዲያዩ የሚያስችል ስራ ተከናውኗል ። በተለይም ከአራዳ ክፍለ ከተማ ከቁርጡሚ ወንዝ ዳርቻ ለተነሳችሁ፣ በሶስተኛ ወገን ክርክር ምክንያት ስትንገላቱ የቆያችሁ ዛሬ ችግሩን ፈተን የመኖሪ የቤት ስላገኛችሁ እጅግ ደስተኞች ነን፤ እንኳን ደስ አላችሁ። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ! ክብርት ከንቲባ Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ

image
image
image
image