image
image
image
image
image

የልደታ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት የመሬት እና ግንባታ ጉዳዮች ዘርፍ ኮሚቴ የመስክ ምልከታና ሱፐርቪዥን አካሄደ፡፡

ታህሳስ 7, 2017
የልደታ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት የመሬት እና ግንባታ ጉዳዮች ዘርፍ ኮሚቴ የቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤት ላይ ሱፐርቪዥን እና መስክ ምልከታ አካሂዷል፡፡ የተከበሩ አቶ ታደሰ ገብሬ የመሬት እና ግንባታ ጉዳዮች ዘርፍ ኮሚቴ ሰብሳቢ ተቋሙ ከዚህ ቀደም ከነበረው አሰራር በብዙ መልኩ የተለወጠ መሆኑን እና የቤት ጥያቄ ይዘው የሚመጡትን ደንበኞች ሳይጉላሉ እንዲስተናገዱ በየወረዳ የነበረውን አገልግሎት ፕሮግራም በማውጣት በየቀጠናቸው በተያዘላቸው ቀን እንዲመጡና እንዲስተናገዱ መደረጉ የሚበረታታ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ የቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤት አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን በወረዳ 189 ባለሙያ ይሰጥ የነበረውን አገልግሎት በክፍለ ከተማ አንድ ማዕከል ከሆነ በኋላ ቴክኖሎጂን ተግባራዊ በማድረግ 21 ባለሙያዎችን በመጠቀም የተቀላጠፈ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን እና ብልሹ አሰራርን የማስቀረት ስራ መሰራቱን የፅ/ቤቱ ሃላፊ አቶ ገመቹ ጌታቸው ገልፀው ምክር ቤቱ የሚያደርገው ክትትል እና ቁጥጥር ውጤታማ በመሆኑ ድጋፉ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል በማለት ተናግረዋል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለም ዘርፍ ኮሚቴው በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 የሚገኘውን ባለ 25 ወለል እና በወረዳ 6 ባለ 4 ወለል በበጎ ፍቃድ እየተገነቡ ያሉትን ህንፃዎች በመስክ ምልከታ የተመለከተ ሲሆን በምልከታውም በበጎ ፍቃድ የሚሰሩት ህንፃዎች ከታሰበው በላይ ውጤታማ መሆናቸውን ክቡር ሰባሳቢው አንስተው መንግስት የድሃውን ማህበረሰብ የቤት ጥያቄ በአጭር ግዜ መፍታት እንደሚችል ማሳያ ነው በማለት ተናግረዋል፡፡ የቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤት አገልገሎትን የተቀላጠፈ ለማድረግ ቴክኖሎጂን ተግባራዊ እያደረገ ቢሆንም አሁንም ከስራ ሰዓት በፊት በጠዋት የሚመጡ ባለጉዳዮች ስላሉ ተከታትሎ መፍትሄ መስጠት ይኖርበታል በማለት የተከበሩ አቶ ታደሰ ገብሬ ተናግረዋል፡፡

መልዕክትዎን ይላኩ