#

ወ/ት ማርታ ፈይሳ
የቤት ልማት ስራዎች ድጋፍ ቡድን መሪ

14 Sep 2025

በቡድኑ የሚሰጡ የአገልግሎት አይነቶች

ከተላለፉ አምስት አመት በሞላቸዉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ አምስት አመት ስለመሙላቱ የሚቀርብ የማስረጃ ጥያቄን ተቀብሎ ምላሽ የመስጠት አገልግሎት፣

ከተገልጋይ የሚጠበቅ ቅድመ ሁኔታ

   የኦርጂናል እና ኮፒ ውል ሰነድ ማቅረብ፣

የባንክ እዳ መዝጋታቸውን የሚገልፅ ማስረጃ፣

የተገልጋይን ማንነት የሚገልፅ የታደሰ መታወቂያ፣

ጥያቄው የሚቀርበው በተወካይ ከሆነ ግልፅ የውክልና ሰነድ ማቅረብ፣

በተላለፉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ ከፍርድ ቤት የሚመጡ የማስረጃ ጥያቄዎችን ተቀብሎ ምላሽ የመስጠት አገልግሎት፣

ከተገልጋይ የሚጠበቅ ቅድመ ሁኔታ

የፍርድ ቤት ተዕዛዝ፣

የፍርድ ባለመብትን ማንነት የሚገልፅ የታደሰ መታወቂያ፣

ጥያቄው የሚቀርበው በተወካይ ከሆነ ግልፅ የውክልና ሰነድ ማቅረብ፣

በተላለፉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ የሚቀርቡ የዉሃና የመብራት አገልግሎቶችን ተቀብሎ ምላሽ የመስጠት አገልግሎት፣

ከተገልጋይ የሚጠበቅ ቅድመ ሁኔታ

የውል ሰነድ ኦርጂናል እና ፎቶ ኮፒ፣

የቁልፍ መረከቢያ ደብዳቤ፣

የተገልጋይን ማንነት የሚገልፅ የታደሰ መታወቂያ ማቅረብ፣

ጥያቄው የሚቀርበው በተወካይ ከሆነ ግልፅ የውክልና ሰነድ ማቅረብ፣

የኢነርጂ ምንጮችና ቴክኖሎጂዎችን የማስተዋወቅና አጠቃቀሙን የማስረጽ ስራ መስራት

ከተገልጋይ የሚጠበቅ ቅድመ ሁኔታ

በአካል ተገኝቶ መሳተፍ

መልዕክትዎን ይላኩ