#

አቶ ግርማ ሲሶ
የይዞታ ጥበቃና ልማት ተነሺ ክትትል ቡድን መሪ

14 Sep 2025

በቡድኑ የሚሰጡ የአገልግሎት አይነቶች

በኪራይ የተሰጡ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን የኪራይ ውል ማደስ አገልግሎት፣

ከተገልጋይ የሚጠበቅ ቅድመ ሁኔታ

ቀደም ሲል የነበረ ውል፣

ወቅታዊ ኪራይ የተከፈለበት ደረሰኝ፣

የታደሰ ህጋዊ የነዋሪነት መታወቂያ፣

ከሚሰራበት ተቋም በስራ ላይ ያለ ስለመሆኑ፣

ከሚኖሩበት የጋራ መኖሪያ ቤት፣

ማህበራት ቤቱ እየኖሩበት ስለመሆኑ ማስረጃ፣

የአደራ እና የማካካሻ ጥያቄዎችን ተቀብሎ መመሪያው በሚፈቅደው መሰረት ምላሽ የመስጠት አገልግሎት፣

ከተገልጋይ የሚጠበቅ ቅድመ ሁኔታ

በአደራ ወይም በማካካሻ ቤት በአዋጁ ያልተወረሰ መሆኑን በሰነድ ወይም በደብዳቤ ተረጋግጦ ከሚመለከተው አካል የቀረበበት ማስረጃ

የቀድሞ የግል ቤቱን የመንግስት ቤቶች ለማስተዳደር ስልጣን ለሰጠው አካል በማካካሻ ወይም በአደራ ማስረከቡን የሚገልፅ ቅፅ ወይም ሰነድ

በማካካሻ የተሰጠው ቤት በአሁኑ ስዓት በእጁ የሚገኝ እና እየተገለገሉበት ያለ መሆኑን የሚያረጋግጡበት ማስረጃ

በማካካሻ የተሰጠውን ቤት የመንግስት ቤቶችን ለማስተዳደር ስልጣን ከተሰጠው አካ መረከቡን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ

ቤቱ በልማት የፈረሰ ከሆነ ይህንን የሚያረጋግጥ ቤቱን ከሚያስተዳድረው አካል ማስረጃ

የባለጉዳዮችን አቤቱታ በመቀበል የጥያቄውን አግባብነት ከመመሪያ አንፃር በማጣራት ምላሽ የመስጠት አገልግሎት፣

ከተገልጋይ የሚጠበቅ ቅድመ ሁኔታ

ቅሬታቸውን በየደረጃው አቅርበው የተሰጣቸው የፁሁፍ ምላሽ

የቅሬታቸውን ጭብጥ በፁሁፍ

ቅሬታቸውን ሊያስረዳ የሚችል ተጨማሪ ሰነዶች

ከመንግስት ቤቶች ጋር ተያይዞ ከተለያዩ አካላት የሚቀርቡ ክሶችን በመቀበል መረጃዎችን በማጣራት ምላሽ የመስጠት አገልግሎት፣

ከተገልጋይ የሚጠበቅ ቅድመ ሁኔታ

የክስ ደብዳቤ፣

የክሱን ጭብጥ የሚያሳዩ ማስረጃዎች፣

መልዕክትዎን ይላኩ